ሉናር ኢንተርናሽናል ኮሌጅ 343 በመጀመሪያ እና በሁለተኛ (ማስተርስ) ዲግሪ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ጳጉሜ 5/2015 ዓ.ም በስካይላይት ሆቴል አስመረቀ።

በ2011 ዓ.ም ተመስርቶ ወደመማር ማስተማር ሥራ የገባው ኮሌጁ ተመራቂዎች በፋይናንስና ኢንቨስትመንት፣ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽንና በፕሮጀክት ማኔጅመንት በማስተርስ ዲግሪ እንዲሁም በማርኬቲንግ ማኔጅመንትና በአካውንቲንግና ፋይናንስ የመጀመሪያ ድግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች አስፈላጊውን መስፈርት ሁሉ በሚገባ አሟልተው ለመመረቅ ብቁ ሆነው የተገኙ ናቸው።

ዶ/ር ታሪኩ አቶምሳ (አሶስዬት ፕሮፌሰር)

የሉናር ኢንተርናሽናል ኮሌጅ ኘረዝደንት በምረቃ መርሐግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር የዘንድሮው ዓመት የምረቃ ፕሮግራም ካለፉት በተወሰነ ደረጃ የተለየ የሚያደርገው የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ለማስመረቅ መብቃታችን ሲሆን፣ በተለይም ለሁላችሁም ግልጽ እንደሆነው የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው አዲስ መመሪያ መሰረት በመጀመሪያ ዲግሪ ለመመረቅ ከፊል መስፈርት የሆነውን የመውጫ ፈተና መውሰድና ማለፍ ነበረባችሁ። በዚህም መሰረት ኮሌጃችን ተማሪዎች ለዚህ ፈተና ብቁ እንዲሆኑ ብርቱ ተግባሮችን አከናውኗል።

በዚህም መሰረት 

100% የማርኬቲንግ ማኔጅመንት ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን ያለፉ ሲሆን በአማካይ 60% የሚሆኑት የሉናር ኢንተርናሽናል ኮሌጅ ተማሪዎችህ የመውጫ ፈተናውን አልፈዋል። ስለዚህ በኮሌጃችን ተማሪዎች የተመዘገበው ውጤት የትምህርት ጥራትንና ስኬትን የሚያመለክት አበረታች ተግባር ነው ብለን እናምናለን “ብለዋል።

አቶ ዘካሪያስ አሰፋ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክትል ዋና ጸሃፊ (Deputy General Secretary)፣ የክብር እንግዳ ሆነው በዚህ የተማሪዎች የምረቃ ሥነስርዓት ላይ  ከመገኘታቸውም በተጨማሪ  አቶ አንተነህ እውነቱ የኮሌጁ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢን ጨምሮ

የኮሌጁ ሴኔት አባላት፣ መምህራን፣ የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

 ምረቃ መርሐግብር በትምህርታቸው ብልጫ ላሳዩ ተማሪዎች እውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷል።

Share your love

Leave a Reply