ማስታወቂያ የምረቃ ፅሑፍ ፕሮፖዛል ፈተና (Defense) በዝግጅት ላይ ላላቹ ተማሪዎች በሙሉ

የምረቃ ፅሑፍ ፕሮፖዛል ፈተና (Defense) በዝግጅት ላይ ላላቹ ተማሪዎች በሙሉ

  1. የፕሮፓዛል ወይም የመመረቂያ ፅሑፍ ፈተና (defense) በምትፈተኑ ጊዜ ፈታኞች የሚሰጡትን አስተያየት ተፈታኝ ተማሪ ማስታወሻ መያዝ ግዴታው ሲሆን ከያዘው ማስታወሻ በመነሳት የማስተካከያ ሥራዎችን የሚሰራ ይሆናል። ነገር ግን ፈታኞች ለኮሌጁ ትምህርት ወይም አይ.ሲ.ቲ. ክፍሎች የሚልኩት ግብረ መልስ/feedback or comment) ካለ ለተማሪው የምንልክ ሲሆን ተማሪው ግን አልተላከልኝም ብሎ እንዳይዘናጋ እናሳስባለን። ተማሪው በያዘው ማስታወሻ የመመረቂያ ፅሑፉን ማዘጋጀት አለበት።
  2. የፕሮፖዛል ወይም መመረቂያ ፅሑፍ ውጤትን በተመለከተ ቅሬታ ማቅረብ የሚቻለው የፈተናው/defense/ ቀን ወይም ከፈተናው ቀጥሎ ባሉት ሁለት የስራ ቀን ብቻ ነው። ቅሬታ ማቅረቢያ ቅፁን መሙላት ግዴታ ነው።

3.ሰሞኑን መብራት በተደጋጋሚ ስለሚጠፋ ላብቶፕዎ ቢያንስ ለአንድ ሰዓት ሊያሰራ የሚችል ሀይል ሊኖረው ይገባል። እንዲሁም በVGA ወይም HDMI እንደሚሠራ ያረጋግጡ።

Share your love

One comment

Leave a Reply