ሜሪጆይ ኢትዮጵያና ሉናር ኢንተርናሽናል ኮሌጅ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚከፍቷቸው ሱቆች የመግባቢያ ሰነድ ተፈራራሙ::

ሜሪጆይ ኢትዮጵያና ሉናር ኢንተርናሽናል ኮሌጅ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚከፍቷቸው ሱቆች “Mary Joy Shops Project” በዛሬው ዕለት በካፒታል ሆቴል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራራሙ። በዝግጅቱ ላይ የሜሪ ጆይ መስራች ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ፣ የኮሌጁ ቦርድ ሰብሳቤ ፣ የኮሌጁ ፕሬዚደንት፣ የኮሌጁ የምርምር ህትመትና እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚደንትና 24 የተለያዩ ሜዲያዎች ተገኝተዋል። በዚህ ፕሮጀክት በአምስት ዓመት ውስጥ 100 ሱቆችን ለመክፈት ዕቅድ ተይዟል። የፕሮጀክቱ ዓላማ አቅመ ደካሞች አረጋውያንና በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች ተደራሽ ማድረግ ይሆናል።

Share your love

One comment

Leave a Reply